`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 67/2012 ህግ የተቋቋመ ቢሮ ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሁለት ዘርፍ ማለትም የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍና የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ተደራጅቶ የሚገኝ ተቋም ሲሆን የከተማው የንግድ ስርዓት ፍትሃዊ እንዲሆንና የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት የጋራ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

የንግድ ጽ/ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ሆኖም የህብረተሰቡን የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር በርካታ ያልተወጣናቸው ችግሮችና እጥረቶች እንዳሉ መረዳት ይቻላል፡፡

ጽ/ቤቱ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና ለማቀላጠፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ተገልጋዮች ወደ ጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት፤ የሚወስደውን ጊዜ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸው ወጪና እንዲሁም በእነርሱ በኩል ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመላከተ የተገልጋዮች ቻርተር ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የከተማዋን የህዝብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ለቀጣይ ሁለት የስትራተጂክ ዘመናት ሊኖር የሚችለውን የህዝብ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህንን ሊሸከም የሚችል የማህበራዊ ተቋማት ለመገንባት፤
  2. ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
  3. አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣
  4. በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡
  5. ሁሉም ተገልጋዮች በስራ ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት ጥቆማና ማናቸውንም ግብዓት በነጻነት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ለመተግበር ነው፡፡

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች (Starategic Themes)

  1. የንግድ ስርዓቱን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከደላላ ትስስር የተላቀቀ በማድረግ ገበያን ማረጋጋት ቀልጣፋንና ተደራሽ የንግድ አሰራር ማስፈን
  2. የህግ ሥርዓቱን በማጠናከር ህጋዊ አሰራርን ማክበርየህግ

ስትራቲጂያዊ ውጤት /Strategic Result/

  1. የሸማቹና የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት
  2. ዘመናዊና ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
  2. ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
  3. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
  4. ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
  5. ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
  3. ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
    ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት