የተቋሙ ስልጣን ፤ ተግባርና ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
የንግድና ገበያ ልማት ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ ከተማ አቀፍ ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፣ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣
የከተማው የምርት ውጤቶች እንዲታወቁ ያደርጋል፣ አውደ-ርዕይ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ይሳተፋል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣
በከተማው ውስጥ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲቋቋም ያበረታታል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤
የገበያ ማዕከላት ያለማል፤ ደረጃ ያወጣል፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን ይቆጣጠራል፤ የሚስፋፉበትንና የሚያድጉበትን ስልት ይቀይሳል፤
የፍጆታ ምርቶችን የአገልግሎት ዘመንና የተዘጋጁባቸውን ንጥረ-ነገሮች ይዘት ሸማቹ ማወቅ በሚችልበት ሁኔታ መሆኑን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
የገበያ ዋጋ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማቀነባበር ተግባራትን ያከናውናል፤ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅም ላይ ያውላል፤
ለገበያ አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን ይቆጣጠራል፤ ያስተዳድራል፤ የአገልግሎት አስጣጡን በተመለከተ መመሪያ ያወጣል፤
ኢ-መደበኛ ንግድ ወደ መደበኛ ስርዓት የሚገባበትን አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
ሕገ-ወጥ ንግድን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች /Strategic Themes/
- የንግድ ስርዓቱን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከደላላ ትስስር የተላቀቀ በማድረግ ገበያን ማረጋጋት ቀልጣፋንና ተደራሽ የንግድ አሰራር ማስፈን
- የህግ ሥርዓቱን በማጠናከር ህጋዊ አሰራርን ማክበርየህግ
ስትራቲጂያዊ ውጤት /Strategic Result/
- የሸማቹና የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት
- ዘመናዊና ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት