በልደታ ክ/ከተማ የንግድ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች
- 1. በሸማች መብት ጥበቃ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- ከጤና መስፈርቶች ወይም ከአዋጅ ጋር የማይጣጣሙ ሀሰተኛና አሳሳች የንግድ ማስታወቂያዎችን ቅድመ- መከላከልና ማረም
- የሸማቾችን መብትና ጥቅም የሚጎዱ የንግድ አሰራሮችን መከታተል፣ መረጃ መሰብሰብና መተንተን፣
- በተለዩ የሸማቾችን መብትና ጥቅም የሚጎዱ የንግድ አሰራሮች ላይ መረጃዎች በመሰብሰብና በመተንተን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ ፡፡
- ሸማቾች የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማጣራትና መፍታት፣
- የሸማች መብት ጥሰቶች እና የተከለከሉ ድርጊቶችን ላይ ክትትል በማድረግ የሸማቹን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፣
- በክትትል የተለዩ የሸማቾችን መብትና ጥቅም የሚጎዱ የተከለከሉ የንግድ አሰራሮች መከታተል መረጃ መሰብሰብ እና መተንተን
- በተለዩ የሸማቾችን መብትና ጥቅም የሚጎዱ የንግድ አሰራሮች ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ
- 2. በኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች ስርጭት ክትትል ቁጥጥር ማካሄድ፤
- 3. በንግድ ግብይት ማስፋፊያ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- መሠረታዊ ሸቀጥ የሚያገኙ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የተማሪ ምገባ መመዝገብና ትስስር መፍጠር፤
- የመሠረታዊ ሸቀጥ ትስስር ለተደረገላቸው ነዋሪዎችና የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስርጭት ማካሄድ
- በቅዳሜና እሁድ ገበያ - መስፈርቱን የሚያሟሉ አቅራቢዎችን /ነጋዴዎችን ወደ
ገበያ እንዲገቡ መጋበዝ
- ለበዓላት የባዛር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለበዓል የሚሆኑ የፍጆታ ምርቶች እንዲቀርቡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- በግና ፍየል ከገበያ ማዕከል ውጪ ያሉ ገበያዎች ላይ በመገኘት ሽያጫቸውን ክትትል ማድረግ
- የነጋዴ አደረጃጀትን ማጠናከር እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ማድረግ
- 4. በገበያ መረጃ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- የዘርፍ ማህበራት እና የነጋዴ ፎረሞችን በማደራጀት እውቅና መስጠት፤
- የገበያ ትስስር መፍጠር
- መሰረታዊ ሸቀጦች ትስስርና ስርጭት አገልግሎት
- 5. መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስርአት ማስያዝ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስርአት ማስያዝ ደንብ ቁጥር 184/2017 ተግባራዊ ማድረግ
- መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን መመዝገብ
- ለመደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች የሽግግር ጊዜ ስራ ፈቃድ መስጠት
- መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን እድሳት አገልግሎት መስጠት
- የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ማሻሻያ አገልግሎት መስጠትታቅዶ
- የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ስረዛ አገልግሎት መስጠት
- የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ምትክ አገልግሎት መስጠት
- የሽግግር ጊዜ አድራሻ ለውጥ ማድረግ
- መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን የምክር አገልግሎት መስጠት
- ለመደበኛ ያልሆኑ የጎዳና ላይ ንግድ የሚሆኑ ቦታዎችን መለየት
- የተለዩ ቦታዎችን በግብረሀይሉ ማጽደቅ
- በፀደቀው መነገጃ ቦታዎች ላይ መደበኛ ያልሆኑ የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን በመስፈርቱ መሰረት ወደ ስራ ውስጥ ማስገባት
- 6. በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ደንበኞች አገልግሎት ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት መስጠት፣
- የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎትመስጠት፣
- የንግድ ስራ ፈቃድ ማሻሻያ ማድረግ
- ምትክ የንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት፣
- የንግድ ስራ ፈቃድ መመለስ አገልግሎት መስጠት፣
- የንግድ ስራ ፈቃድ መመለስ አገልግሎት
- የአክሲዮን ማህበራት መመስረቻና መተዳደሪያ ጽሁፍ ዝግጅት ማማከር አገልግሎት
- በአክሲዮን ማህበራት የሚቀርቡ ቅሬታዎች በህጉ መሰረት መደገፍና መከታተል
- በአክሲዎን ማህበራት የቦርድ አባላትና የማኔጅመንት አባላት መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን መፍታት
- የአክሲዎን ማህበራት መተዳደሪያ ደንቦች ላይ በየአመቱ በሚደረጉ ማሻሻያዎችና የቦርድ አመራር ምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት በህጉ መሰረት መከናወኑን መከታተልና መደገፍ
- የግለሰብና የንግድ ማህበር የንግድ ምዝገባ አገልግሎት
- የግለሰብና የንግድ ማህበር የንግድ ምዝገባ ለውጥ መአድረግ
- የግለሰብና የንግድ ማህበር ምትክ የንግድ ምዝገባ አገልግሎት መስጠት ፤
- የንግድ ማህበር የንግድ ምዝገባ ስረዛ አገልግሎት መስጠት፤
- አዲስ የንግድ ስም ምዝገባ አገልግሎት መስጠት፤
- የንግድ ስም ምዝገባ ለውጥ/ ማሻሻያ አገልግሎት ማድረግ፤
- ምትክ የንግድ ስም ምዝገባ አገልግሎት መስጠት፣
- የንግድ ስም ምስክር ወረቀት መሰረዝ