የልደታ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ወለል
+251916873549
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ተቋማዊ አደረጃጀት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
ደንብና መመሪያዎች
ማስታወቂያ
የደንበኞች አገልግሎት
አገልግሎቶች
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
ለማንኛዉም ቅሬታዎ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
ለማንኛዉም ጥያቄዎ
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
መጽሄቶች | Magazines
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
መስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ የበዓል ባዛር መከፈት መቻሉ ተገለፀ።
መስከረም 15, 2018
"በእምርታ እና በማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዛር ተከፍቷል። ባዛሩን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት፣ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ፣ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በቅንጅት አዘጋጅተዋል በባዛር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት ባዛሩ በርካታ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት የቀረቡበት መሆኑንና ባዛሩ የበዓል ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ በመግለፅ የክ/ከተማው ማህበረሰብ በባዛሩ በመገኘት የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበይ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አመት ባዛርን በጥሩ ሁኔታ ካጠናቀቅን በኋላ የመስቀልን በመጀመር ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ ምርቶችን ማቅረብ መቻሉን የገለፁት አቶ አራርሳ አያይዘው ማህበረሰቡ በተዘጋጀው ባዛር የቀረበውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ መገብያየት እንደሚችሉም ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በበኩላቸው ባዛሩ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈተ ሲሆን በባዛሩ የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማካተት በቂ አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰዉ በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የምርት አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት የሚከላከል መሆኑን ገልፀዋል ። በበዛሩ የተለያዩ ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶች ያካተተ ነው ያሉት ወ/ሮ ተስፋነሽ አያይዘው ማህበረሰብ የቀረበውን ምርት እስከ መስቀል ድረስ በባዛሩ ተገኝተው መገበያየት እንደሚችሉ ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ሀምሌ 1, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በመድረኩ እንደገለፁ የንግድና ዘርፍ ማህበራት በኢኮኖሚያዊና ያለው ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ከመንግስት ጎን በመሆን ያሉ ችግሮችን እየፈታን ለውጥና ውጤት ለማምጣት በጋራ እንሰራለን ብለዋል። ማህበሩ ንግድና ኢንቨስትመት እንዲስፋፋ ያበረከተው ሚና ቀላል አይደለም ያሉት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በንግዱ ዘርፍ ተወዳዳሪ በመሆን ነጋዴው በአንድ ተደራጅቶ ያለውን ሀሳብ በማንሳት የንግዱ ሰርፍ የተሻለ ቁመና እንዲኖረው ያስፈልጋል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነት ደረሳ እንደተናገሩት የነጋዴ ማህበረሰብ በምናከናውናቸው ሰው ተኮር ተግባር ላይ የራሳችሁን ሚና በመወጣት ለላፊነታችሁን ተወጥታችኋል በማለት መንግስት ለሚሰበስበውም ግብር ነጋዴው የሚጠበቅበትን በታማኝነት በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ በመክፈል ሀላፊነታችሁን ልትጡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። አገር ከናንተ የምትጠብቀው በርካታ ነገሮች አሉ ያሉት ሀላፊዋ ይህን ደግሞ በመነጋገር በመወያየት በክፍለ ከተማችን ላይ የተሻለ የንግድ ስርዓት እንዲኖር በጋራ እንሰራለን በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፍነሽ በጋሻው እንደተናገሩት በክፍለ ከተማች የሚገኙ በ10ሩ ወረዳዎች ያሉንን ነጋዴዎች የምክር ቤቱ አባል በማድረግ መብታቸውንና ግዴታቸን በአግባቡ ተገንዝበው በአግባብ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ይረዳቸዋል በማለት በሰው ተኮርና በኮሊደር ልማት ከተማችን ውብና ንፁህ እንድትሆን የነጋዴው ሚና ጉልህ ነው በማለት ገልፀዋል። ነጋዴው ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ያላቸውን ሚና ከመወጣት አንፃር እየሰሩ ያሉት ተግባር የላቀ ነው በማለት ወ/ሮ ተስፋነሽ በጋሻው ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ አበበ ነጋዴው የሚጠበቅበትን ግብር ለመክፈል የሚያስችለውን ግንዛቤ በመፍጠር ያለበቸውን ግዴታ በቅድሚያ በመክፈል ሀላፊነችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል። ነጋዴው የምክር ቤቱ አባል በመሆን መንግስት የሰጠውን መብትና ግዴታ በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል ያሉት አቶ ተስፋዬ አበበ ነጋዴው በተሰጠው መብት ተጠቃሚ በማድረግ በፍታዊነት ልሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ተሳታፊዎችም በንግዱ ዘርፍ የተጣለብንን ሀላፊነት በመወጣት የማህበረሰብን ፍላጎት ማሟላት ይገባል በማለት ከኛ የሚጠበቅብንን ግብርም በወቅቱ መክፈል ይገባል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
ሀምሌ 7, 2018
በክ/ከተማችን በሁሉም ወረዳዎች እና በተመረጡ ቦታዎች ላይ 11 የቅዳሜና የእሁድ ገበያ መዳረሻዎች አቋቁሞ የመሰረታዊ ፍጆታ ምርቶች እና የፋብሪካ ምርቶች በስፋት እና በጥራት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪ በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። በነዚህ የቅዳሜና እሁድ ገበያ መዳረሻዎች ከአርሶ አደሩ በቀጥታ የሚቀርቡ ምርቶች እየቀረቡ ሲሆን የምርትቹ ዋጋም ተመጣጣኝ ነው። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ከ11 የቅደሜና የእሁድ ገበያ መዳረሻዎች በተጨማሪ በሸማች ማህበራት በኩልም በተለይ የፋብሪካ ምርት የሆኑ እንደ ስኳር፣ ዘይት እና ዱቄት የመሳሰሉ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ የክ/ከተማው አስተዳደር ባቋቋማቸው እና በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የእሁድ ገበያዎች እንዲሁም የሸማች ማህበራት በመቅረብ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ከአላስፈላጊ ወጪ እንድትቆጠቡ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።
ሀምሌ 8, 2018
የጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በግምገማው ወቅት እንደተናገሩት ባለፈ ዓመት ተቋሙ በርካታ ተግባራት እንዳከናወነ ገልፀው በዚህም በክ/ከተማ በሚገኙ 10 የእሁድ ገበያ ላይ የሰብል፣ ኢንዱስትሪ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ተዋጾ ምርት አቅርቦት መሠረት በማድረግ ውጤታማ ስራ እንደተሰራ ገልፀዋል። ኃላፊዋ አክለውም በህብረት ሥራና ሸማች ማህበራት የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎችንና ምርቶች የመሰብሰብ፣ የመከዘንና የማከመቻት ስራ ፥በንግድ ስራ ድርጅት አማካይነት የድጎማ ምርት በማቅረብ ለማህበረሰብ ስርጭት ማካሄድ ባለፈ ዓመት በውጤታማነት የተሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ከከተማ ጀምሮ እስከ ወረዳ የህገ -ወጥ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ተዋቅሮ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ በዚህም ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ከአድራሻ ውጪ የሚሰሩ፣ ከተሰጣቸው ዘርፍ ውጪ የሚሰሩ፣ የጥራት ችግር ያለባቸውን ምርቶች የሚያቀርቡ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ፣ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ፣ ምርት የሚያከመቹ መጋዘን የመፈተሽ ስራ ተሰርቷል እርምጃ የመውሰድ መከናወኑን ተናግረዋል። ወ/ሮ ተስፋነሽ አክለውም በ 2017 ዓ.ም አፈፃፀማችን እቅድን መሠረት አድርጎ ከመፈፀም አንፃር ተቋሙ ያለበት ሁኔታን በርካታ ተግባራት እንዳከናወነ በመግለፅ በክፍተት የታዩትን በቀጣይ በማስተካከል አሁን ካለን አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ እንዲሆን በቅንጅት በትስስር መስራት አለብን በማለት ገልፀዋል። በተደረገው የድጋፍና ክትትል ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሮ ውጤት በማምጣት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚችል ተቋም መገንባት ችለናል በማለት ገልፀዋል ኃላፊዋ። የመድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ልክ ውይይት መደረጉ የተሻለ ሲሆን በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ እንዲሆን በጋራ መስራት ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር አሁን ያለውን አለም አቀፋዊ የኑሮ ውድነት ለማርገብ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
ሰኔ 28, 2018
ነዋሪዎችን ካልተገባ ወጭና እንግልት የታደገው ገበያ ። ከነዚህ ተግባራት ውስጥ አንዱ ደግሞ የእሁድ ገበያን ተደራሽነት ማስፋትና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ማስቻል ነው። አስተዳደሩ 11 የእሁድ ገበያ መዳረሻ ስፍራዎች በማዘጋጀት ማህበረሰቡ ምርቶችን በሚቀርበው ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዛ አስችሏል። የምርት እጥረት እንዳይከሰትም የገበያ ትስስርን በመፍጠር ምርቶች ከገበሬውና ከአምራች ኢንዱስትሪዎች በቀጥታ ለሸማቹ እንዲቀርቡ አድርጓል እያደረገም ነው። ማህበረሰቡም የእሁድ ገበያ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ከህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ብዝበዛ ተላቋል። ሸማቹ ምርት ለመግዛትም ሆነ የገዛውን ምርት ለማስጫን ለትራንስፖርት ያወጣው የነበረን ወጭም መቀነስ ተችሏል ። እርስዎስ ዛሬ እረፍትዎም አይደል በአቅራቢያዎ ባለው የእሁድ ገበያ ጎራ ብለው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይግዙና የእሁድ ገበያን ቱርፋት ያጣጥሙ እንላለን። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
ዜና | Oduu | News
የንግድ ተቋማት የምሽት ስራ ጉብኝትና የቁጥጥር ስራ ተካሄደ።
ሰኔ 24, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ስር የሚገኙ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 ድረስ እንዲሰሩ የወጣው ደንብ ቁጥር 185/2017 አስመልክቶ የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል ለንግድ ተቋማቱ ግንዛቤ እና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል በቁጥጥር ተግባሩ ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው እና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ደሳለኝ ካሴ በተገኙበት ተካሂዷል። በምሽት የንግድ አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ቁጥር 185/2017 አስመልክቶ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል አባላት በጋራ በመሆን በወረዳ ውስጥ ተዘዋውረው ምልከታና ቅኝት አድርገዋል:: በምሽት የንግድ አገልግሎት እንዲሰጥ የተፈለገው የከተማዋን ፈጣን እድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ በሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ጥራት ያላቸው ምርቶች የኢንዱስትሪና የግብርና በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርበዋል።
መጋቢት 21, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ና የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በልደታ ክ/ከተማ የቅዳሜና እሁድ ገቢያዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የኢድ-አል ፈጥር በዓል አስመልክቶ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርት የሆነው የዘይት አቅርቦት ምርቶች በሰፊው ቀርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት በገበያዎቹ ባደረግነው ቅኝት የግብይቱ ሁኔታ ፥ የዘይት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ ና በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ተናግረው ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በብዛት ቀርበዋል ሲሉም ተናግረዋል።
ዜና | Oduu | News
የተረጋጋ የንግድ ስርዓትን ለማስፈን የምርት አቅርቦቾችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው እየቀረበ ነው።
ጥር 24, 2018
የገና በዓልን አስመልክቶ ለክፍለ ከተማ ነዋሪ በ1ዐሩ ወረዳዎች በእሁድ ገበያ ባዛር በመክፈት የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትንና የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት ስራን በትኩረት እየተሰራ ሲሆን ባዛሮች ለተከታታይ ቀናት ክፍት በማድረግ ለሸማቹ ተደራሽነትን በማስፋትና የምርት አቅርቦትን መጠንን በማሳደግ ለህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በመሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭትን አሰመልክቶ ባሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የካቲት 18, 2018
በውይይቱ ነዋሪዎች፣ የምክር ቤት አባላት ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ንግድ ባለሙያዎችና የመሰረታዊ ፍጆታ አቅራቢ ድርጅት ማኬባ ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በመሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በተለይም ስኳርና ዘይት ስርጭት ላይ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለይቶ መፍትሄ በማስቀመጥ የሸማቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል። ዶ/ር ጥበቡ አክለውም የመሰረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሰፍን በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች አቅርቦትን የማሻሻል እና የቁጥጥር ስራውን የማጠናከር ስራ መሰራቱንም ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በምርቶች ስርጭትና አቅርቦት ላይ ያሉ ክፍተቶች ለመሙላት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ባህል ሆኖ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! http://linktr.ee/lidetacommunication1
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወር ውጤታማ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ።
የካቲት 11, 2018
ጽ/ቤቱ ለወረዳ ንግድ ጽ/ቤቶችና ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ ፈፃሚዎች የ2017 በጀት ዓመት የ6ወር አፈፃፀም ምዘናን መነሻ በማድረግ ዋንጫ እና ሰርቲፊኬት ሰጥቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በእውቅናው ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት እውቅናው ለቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ስንቅ ይሆናል ብለው የተሻለ ውጤት ያስመዘገባቹህ ፈፃሚዎች እና ወረዳዎች እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በምዘና ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስንነቶች ደግሞ እንዲታረሙ በቀሪ ወራት መስራት ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው በንግድ ስርዓት በአቅርቦትና በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር በማጠናከር የህብረተሰብ እርካታ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጌታሁን ሀ/ማሪያም ባስተላለፍት መልዕክት በቀጣይ የንግድ ስርዓቱን በማሻሻል የማህበረሰቡን እርካታ የበለጠ ለማሻሻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል በማለት ለተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላቹህ ብለዋል። በእውቅናው ወረዳ 8 ንግድ ጽ/ቤት 1ኛ ወረዳ 9 ንግድ ጽ/ቤት 2ኛ ወረዳ 1 ንግድ ጽ/ቤት 3ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! https://t.me/lideta_subcity https://www.facebook.com/lidetapress https://youtube.com/@lidetasubcitycommunication1772?si=xLUnaghDDIS66G-c https://www.tiktok.com/@lideta_subcity?_t=ZM-8trzUREMKaj&_r=1
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በንግድ ተቋማት በጥናት በተለዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር፣ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና በ2017 በቀሪ 6 ወራት ዕቅድ ክለሳ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ጥር 28, 2018
በውይይቱ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በጥናቱ የተለዩ በንግድ ተቋማት ያሉ ብልሹ አሰራሮችን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለይተን አፋጣኝ መፍትሄ ለማስቀመጥና ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ነው ብለዋል። በቀጣይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር ፍትሃዊ የንግድ ሥርዓትን የማስፈን ስራ ይከናወናል ያሉት ኃላፊው የንግድ ተቋማት በር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ፣ የንግድ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና የህጋዊ ስነ-ልክ መሳሪያዎች ትክክለኛነት ማረጋገጥ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣ የእሁድ ገበያ ምርት አቅርቦት እና ተደራሽነት ማስፋት በትኩረት የሚሰሩ ይሆናሉም ሲሉ ገልፀዋል። የተቋሙን አመራርና ፈጻሚዎችን በአመለካከትና በክህሎት የማብቃት ስራ መስራት በተቋሙ የሚገኙ ግብዓቶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም፣ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ፣ ችግር ፈቺ ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረ መልስ ሥርዓትን መተግበር፣ ተቋሙን ለአገልጋና ለተገልጋይ ምቹ የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚሰራም በመድረኩ ተጠቁሟል። የጥናት ሰነድ ያቀረቡት የከተማ ንግድ ቢሮ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳሬክተር አቶ ቲቶ ናቸው።
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
የዛሬይቱ ልደታ
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ያግኙን
lidetatrade@gmail.com
+251916873549