peace logo     በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ አ/ጽ/ቤት

ሰላም ለሁሉም

እውነተኛ ሰላም የሚገኘው በልዩነቶቻችን ውስጥ አንድነትን እና መከባበርን ስንገነባ ነው።

የሀገር ደህንነት

የህዝባችን ደህንነት አስተማማኝ የሚሆነው በጋራ መደጋገፍና በህግ የበላይነት ላይ ሲመሰረት ነው።

የሰላም ሰራዊት

ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፋት ታላቅ ስጦታ በሰላምና በፀጥታ የከበረች አገር ናት።

ራዕይ (Vision)

በ2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት።

ተልዕኮ (Mission)

በክ/ከተማችን የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤ የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባለቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው።

እሴቶች (Values)

ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት፣ ታማኝነት፣ ግልጽነት፣ ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት ፣ የህግ የበላይነት፣ የጋራ ተሳትፎ እና ለህዝብ ደህንነት ቅድሚያ መስጠት መሰረታዊ መርሆቻችን ናቸው።