image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በንግድ ተቋማት በጥናት በተለዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር፣ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና በ2017 በቀሪ 6 ወራት ዕቅድ ክለሳ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

ጥር 28, 2018
በውይይቱ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በጥናቱ የተለዩ በንግድ ተቋማት ያሉ ብልሹ አሰራሮችን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለይተን አፋጣኝ መፍትሄ ለማስቀመጥና ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ነው ብለዋል። በቀጣይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር ፍትሃዊ የንግድ ሥርዓትን የማስፈን ስራ ይከናወናል ያሉት ኃላፊው የንግድ ተቋማት በር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ፣ የንግድ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና የህጋዊ ስነ-ልክ መሳሪያዎች ትክክለኛነት ማረጋገጥ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣ የእሁድ ገበያ ምርት አቅርቦት እና ተደራሽነት ማስፋት በትኩረት የሚሰሩ ይሆናሉም ሲሉ ገልፀዋል። የተቋሙን አመራርና ፈጻሚዎችን በአመለካከትና በክህሎት የማብቃት ስራ መስራት በተቋሙ የሚገኙ ግብዓቶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም፣ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ፣ ችግር ፈቺ ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረ መልስ ሥርዓትን መተግበር፣ ተቋሙን ለአገልጋና ለተገልጋይ ምቹ የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚሰራም በመድረኩ ተጠቁሟል። የጥናት ሰነድ ያቀረቡት የከተማ ንግድ ቢሮ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳሬክተር አቶ ቲቶ ናቸው።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች