image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወር ውጤታማ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ።

የካቲት 11, 2018
ጽ/ቤቱ ለወረዳ ንግድ ጽ/ቤቶችና ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ ፈፃሚዎች የ2017 በጀት ዓመት የ6ወር አፈፃፀም ምዘናን መነሻ በማድረግ ዋንጫ እና ሰርቲፊኬት ሰጥቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በእውቅናው ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት እውቅናው ለቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ስንቅ ይሆናል ብለው የተሻለ ውጤት ያስመዘገባቹህ ፈፃሚዎች እና ወረዳዎች እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በምዘና ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስንነቶች ደግሞ እንዲታረሙ በቀሪ ወራት መስራት ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው በንግድ ስርዓት በአቅርቦትና በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር በማጠናከር የህብረተሰብ እርካታ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጌታሁን ሀ/ማሪያም ባስተላለፍት መልዕክት በቀጣይ የንግድ ስርዓቱን በማሻሻል የማህበረሰቡን እርካታ የበለጠ ለማሻሻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል በማለት ለተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላቹህ ብለዋል። በእውቅናው ወረዳ 8 ንግድ ጽ/ቤት 1ኛ ወረዳ 9 ንግድ ጽ/ቤት 2ኛ ወረዳ 1 ንግድ ጽ/ቤት 3ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !! https://t.me/lideta_subcity https://www.facebook.com/lidetapress https://youtube.com/@lidetasubcitycommunication1772?si=xLUnaghDDIS66G-c https://www.tiktok.com/@lideta_subcity?_t=ZM-8trzUREMKaj&_r=1

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች